ታሪካችን ባአጭሩ
በ1990ዎቹ መጨረሻ አካባቢ አባቴ በበርሊን ቀዳሚ ከተሰኙት አንዱ የሆነውን የኢትዮጵያ ባህላዊ ምግብ ቤት በበርሊን ከተማ ፕሬንስላዋ በርግ ዕምብርት ላይ ከፈተ።
ከተለያዩ የዓለም ክፍሎች እየመጡ በደስታ አብሮነታቸውን ይጋሩ ለነበሩት ጓደኞች፣ ቤተሰቦችና፣ እንግዶችን መታሰቢያ ይሆን ዘንድ በትውልድ ከተማዬ በበርሊን ይህንን የኢትዮጵያን የባህል አመጋገብ ለማስተዋወቅና በሰዎች ዕይታ ውስጥ እንዲገባ ቆረጥሁ።
ልዩ የሆነው ኮምጣጣ የእንጀራ ጣዕም፣ የበርካታ ቀናት የቡኮ መብላላት ውጤት ነው። የእንጀራው ሊጥ በባህላዊው የሸክላ ምጣድ ላይ ወደ ለምለም እንጀራንት ይቀየራል።
የእንጀራ ጥራት መለኪያ በላዩ ላይ የሚታዩት ጠቃጠቆዎች ወይም ዓይኖች ናቸው። የኢትዮጵያ ባህላዊ ምግብ ውስጥ እንጀራ ልዩ ልዩ የሆኑ ወጦችን ለማባያነት ያገለግላል።
በማዕድን ይዘቱ እጅግ የበለጸገው እንጀራ እንደ መካከለኛው አውሮፓ ዳቦ አልሚ የሆነ የምግብ አማራጭ ነው። እንጀራችን ከእንስሳትና ከእንስሳት ተዋዕጾ ከግሉት፣ እና ላክቶስ (vegan, gluten, lactose) ከሚሰኙ ንጥረ ነገሮች ነጻ ሲሆን ለብዙው የሕብረተሰባችን ጤናማነቱ ተመራጭ ያደርገዋል።
እንጀራ ለስላሳ እና ኮምጠጥ ያለ ከጤፍ የሚመረት ከጤፍ ዱቄት (የሣር ዝርያ) በጣም ስስ ዳቦ ነው። በኢትዮጵያ እና በኤርትራ በባህላዊ ምግብነት ይታወቃል። የጤር ዱቄቱ በውሃ ርሶ ወደ ሊጥነት የሚለወስ ሲሆን ለተወሰኑ ቀናት ኩፍ እንዲል መቆየት ይኖርበታል።
በጋለ የሸክላ ምጣድ ላይ በስሱ የሚጋገረው እንጀራ እንደፈረንሳዮች ስስ ቂጣ (galette) በቀላሉ በእጅ መበጣጠስ ይችላል። የላይኛው ገጽታው ላይ ያሉት ብዙ ዓይኖች እንጀራው በሚበላበት ጊዜ በውስጣችው ብዙ ወጥ እንዲይዙ ይረዳል።
እንጀራ እንደዋና ግብአትነቱ በጣም ከተለያዩ ምግቦች ጋር ሊቀርብ ከመቻሉም ባሻገር ብዙ ቅመም ከሚዘጋጁ ልንቅጦች እና ወጦች መበላት ይችላል። እንጀራው በቀኝ እጅ በጨቅ ይደረግና ከቀረበው ወጥ ወይንም ልንቅጥ ጠቀስ ተደርጎ እንደየፍላጎቱ ተመጥኖ ይጠቀለልና ይጎረሳል።